በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ራዕይ፦ የአፋር ብ/ክ/መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ለክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት/ካቢኔ/እና አስተዳደራዊ ፍትህ ፈልገዉ ለሚመጡ ዜጎች የተቀነባበረ ሁለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት በመስጠት አፈፃፀሙ ምንም መሰረታዊ ቅሬታ የማይነሳበት አርኪ ደረጃ ደርሶ ማየት፣ ተልዕኮ የክልሉ ር/መስተዳድርና መስተዳድር ም/ቤቱ የተጣለበትን ሐላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል የተቀነባበረ ሁለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፤ የዞን መስተዳድር ፅ/ቤቶች በእቅድ አፈፃፀም ፣በስልጠና፣በአደረጃጀትና በስራ አመራር የሙያ ድጋፍ በመስጠት መልካም አስተዳድርና ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡ እሴቶች፦ • ጥራት ያለዉ ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት እንሰጣለን፣ • መ/ቤቱን የተሻለ ቦታ ማድረስ የኛ ሃላፊነት ነዉ፣ • ለስነ-ምግባር መርሆዎች ተገዥ በመሆን እናገለግላለን፣ • በጋራ የመስራት ባህልን እናዳብራለን፣ • ሙስና የልማት ፀር በመሆኑ እንዋጋለን፣ • ባለን ዉስን ሀብት ትልቅ ዉጤት እናስመዘግባለን፣ • በፆታ እኩልነት እናምናለን፣ • ህዝብን በማሳመን እንሰራለን፣ • የህብረተሰቡን ባህል እናከብራለን፣