Search results for - hosaena

  • South Nation Nationalities and People Regional State Gamo Gofa Zone Administration

    01

    በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት

    046 881 0085
  • በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ደቡብ ኦሞ ዞን ባህል ቱ/መን/ኮሙ/ጉ/መምሪያ

    ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ ክልል ካሉት ዞኖች አንዷ ስትሆን ከባህር ጠለል በላይ 1,490ሜ (4,890ጫማ) ከፍታ ላይ የሚትገኝ ሆኖ በሰሜን ጋሞ ጎፋና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ፣ በደቡብ ኬንያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢሌሚ ትሪያንግል በምዕራብ ቤንች ማጂ በምስራቅ ኦሮሚያ ክልል በሰሜን ምዕራብ ኬፋ፣ በሰሜን ምስራቅ ደራሼና አሌ ወረዳ (ሰገን አካባቢ) ያዋስኗታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 16 ብሔረሰቦችን ያቀፈች ብቸኛ ዞን ደቡብ ኦሞ ናት፡፡ ዞኗ በ8 ወረዳና አንድ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረች፤ በውስጧ በ16 ብሔረሰቦች ገጸ በረከት የታደለች ብቸኛዋ የሀገራችን ህብረ ብሔር ዞን ናት፡፡ ሁሉም ብሔረሰቦች የራሳቸው ባህልና ወግ ያላቸው ሲሆን በመከባበርና በመፈቃቀድ ላይ በተመሠረተ ኑሮ ዘይቤ ለዘመናት ሲኖሩ ከርመዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ባላቸው የባህል እሴቶች የቱርስት መስህብ ከመሆኑም ባሻገር በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግስት የልማት ኮሪደር እየሆነች ትገኛለች፡፡

    046 775 0082
  • የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት

    Arbaminch, Ethiopia

    ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ በብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ከሚገኙ 14 ዞኖች አንዷ ስትሆን ከነዚሁ አቻ ዞኖች በቆዳ ስፋቷ ቀዳሚ ናት፡፡በደቡብ ኬንያ፣በሰሜን ጋሞጎፋ ዞንና ኮንታ ልዩ ወረዳ፣በምዕራብ ደቡብ ሱዳንና ቤንች ማጂ፣በምስራቅ የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞን የደ/ኦሞ ዞንን ያዋስናሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር በክልሉ ከሚገኙት 56 ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 16ቱ የሚገኙባት መሆኗንም ታዋቂ ያደርጋታል፡፡ የዞኑ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ጂንካን ጨምሮ በአንድ ከተማ አሰተዳደር፣ በ2 አርሶ አደርና 6 አርብቶ አደር ወረዳዎቿ በ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መረጃ መሰረት በጠቅላላው 724,183 ህዝብ በመፈቃቀርና በመተሳሰብ የሚኖርባት ዞን ናት፡፡16ቱም ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ህገመንግስቱ ባጎናፀፋቸዉ መብት ተጠቅመው የየራሳቸው ቋንቋ፣ታሪክ፣ባህልና እምነት በመንከባከብና በማስፋፋት እየኖሩ ያሉ ዜጎች ከመሆናቸዉም ባሻገር ልዩነታቸው ለዞናዊ አንድነታቸው ዉበት ፈጥሮላቸዋል፡፡

    046 775 0436
  • ሳውዝ ስፕሪንግ ሆቴል

    የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችና መጠጦችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ባለው ሁኔታ እናቀርባለን:: ይምጡና ይጎብኙን በአገልግሎታችን ይረካሉ::

    0911 759 029
  • በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግስት የካፋ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ

    የካፋ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ በዞኑ ያለውን ምቹ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ እና ታታሪውን የካፋ ሕዝብ በመጠቀም ሕብረተሠቡን ወደ ተሻለ የልማት ጎዳና እና የኑሮ ደረጃ ለማድረስ ጠንክሮ እየሠራ የሚገኝ መምሪያ ነው::

    047 331 0031
  • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጌዲኦ ዞን የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ

    P.O.Box 31
    Governmental Organizations

    046 331 2506
  • በደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መ/ የሀድያ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት

    P.O.Box 206
    Governmental Organizations

    1.2 .የዞኑ አጠቃላይ ገጽታ የሀድያ ዞን በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ሲሆን በ7ዐ3I19II - 7ዐ56I1II ሰሜን ላቲትዩድ እና በ37ዐ23I14II - 38ዐ52I13II ምሥራቅ ሎንግቲዩድ መስመሮች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ በመልክአ ምድራዊ አቀማመጡ በደቡብ ምሥራቅ ከሀላባ ልዩ ወረዳና ኦሮሚያ ክልል፣ በሰሜን ምስራቅ ከስልጤ ዞን፣ በምዕራብ ከየም ልዩ ወረዳና ኦሮሚያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ከከምባታ ጠምባሮና ወላይታ ዞኖች፣ በደቡብ ከወላይታ ዞን እና በሰሜን ከጉራጌ ዞን ጋር ይዋሰናል። የዞኑ የቆዳ ስፋት 4109 ካሬ ኪ.ሜ አካባቢ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 69% የለማ፣ 7.22% ሊለማ የሚችል፣ 7% ለግጦሽ የዋለ፣ 8.78% በደንና ቁጥቋጦና 8% በሌሎች የተሸፈነ ነው፡፡ በ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት ¯Sታ© ¾Q´w ዕÉу 2.9 ŸS„ ሲሆን በዚሁ ስሌት መሰረት በተደረገው ትንበያ የዞኑ ህዝብ ቁጥር በ2002 1,371,625 ይሆናል፡፡ ይህም ከክልሉ ሕዝብ 8.57 በመቶ ድርሻ ይይዛል፡፡ ከዚህ ውስጥ ወንዶች 681,522 /49.69%/ እና ሴቶች 690,103 /5ዐ.31%/ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዞኑ ጠቅላላው ህዝብ 90.23 % በገጠር እና 9.77% በከተማ የሚኖር ነው፡፡ ከጠቅላላው የዞኑ ሕዝብ ውስጥ በአምራች ዕድሜ ክልል /ከ15 - 64/ ከሚገኙ 721,055 ውስጥ ወንድ 348,703 /48.36%/፣ ሴት 372,352/51.64%/፣ አምራች ባልሆነ የዕድሜ ክልል/ ከ0 እስከ 14 ዓመት እና 65 ዓመትና በላይ/ ከሚገኙ 650570 ውስጥ ወንድ 332,819/51.16%/ ሴት 317,751/48.84%/ ይገኛሉ። ይህም ከጠቅላለው ወንድና ሴት ቁጥር ጋር ሲነጻፀር በአምራች ዕድሜ ክልል ያሉ ወንዶች 51.17% እና ሴት 48.83% እንዲሁም አምራች ባልሆነ ዕድሜ ክልል ያሉ ወንዶች 48.83% እና ሴቶች 46.04% ነው። የ7 ዓመት ሕፃነትን በተመለከተ 40464 ይሆናል። በዞኑ ያለው የህዝብ ጥግግት በአማካይ በካሬ ኪሎ ሜትር ሰው ሲሆን ዝቅተኛ የሕዝብ ጥግግት ወረዳ ሆኖ ጥግግቱም በአማካይ በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትርና ከፍተኛ የሕዝብ ጥግግት በሌሞ ወረዳ 5ዐዐ ሰዎች በአንድ ካሬ ኪ.ሜ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ዞኑ ከባህር ወለል በላይ /በሶሮ ወረዳ ጎርጣንቾ አካባቢ/ ከ54ዐ - /ሰንግዬ በዱና ወረዳ/ 2972 ሜትር ከፍታ ያላቸውን ሥፍራዎች ይሸፍናል፡፡ የአየር ንብረት ሁኔታ ሲታይ 19% ደጋማ፣ 68.1% ወይና ደጋና 12.9% ደግሞ ቆላማ ነው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ1ዐዐዐ እስከ 17ዐዐ ሚ.ሜ እና ዓመታዊ የሙቀት መጠኑ ከ1ዐ.40c እስከ 22.5ዐc ይደርሳል፡፡ የዞኑን ሀብትና የአየር ንብረት መሠረት በማድረግ ዞኑ በአራት ንዑሳን አካባቢዎች ተከፍሏል፡፡ በዚሁ መሰረት ዱና፣ ሌሞ፣ ሶሮ፣ አንሌሞ፣ ምሻና ከፊል ጐምቦራ ወረዳዎች እንሰትና ከፍተኛ የስንዴ፣ የጤፍ፣ የገብስና የጥራጥሬ ሰብል ምርት አብቃይ፣ ከፊል ግቤ፣ ከፊል ጐምቦራ፣ ሶሮና ምዕራብ ባደዋቾ ወረዳዎች ከፍተኛ ቡናና ፍራፍሬ ተክሎች አብቃይ፣ ሻሸጐና ምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳዎች ከፍተኛ የቦቆሎ፣ በርበሬና ቦሎቄ ምርት አብቃይ ወረዳዎች፣ እንድሁም የግቤ፣ የሶሮና የጐምቦራ ወረዳዎች ቆላማ አካባቢዎች በከፍተኛ እንስሳት ሀብት ይታወቃሉ፡፡ በተለይ ዞኑ ከፍተኛ የስንዴ ምርት አምራች በመሆኑ ለአካባቢ ፋብሪካዎችና በማዕከላዊ ከተሞች ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በከፍተኛ የጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ይታወቃል፡፡ ዞኑ ለግብርና ልማት ተስማሚ የሆነ የተለያየ የመሬት አቀማመጥ፣ የአየር ንብረትና የአፈር ዓይነት ያለው በመሆኑ ከአዝርዕት ሰብሎች ስንዴ፣ ጤፍና ገብስ፤ ከጥራጥሬ ሰብሎች ባቄላ፣አተርና ቦሎቄ፤ ከአገዳ ሰብሎች ቦቆሎና ማሽላን በስፋት በማምረት ይታወቃል። ከዚህ ባሻገር ለመስኖ ልማት ሊውል የሚችል እስከ 5ዐ46 ሄክታር መሬትና ዓመቱን ሙሉ ከሚፈሱ ወንዞች መካከል ጎምቦራ፣ ዋራ፣ ዳጎባ፣ ግቤ፣ ገሙና፣ አጃቾ፣ ሆብችግታና ልንታላ የመሳሳሉ ወንዞች ይገኛሉ፡፡ የንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት አጠቃላይ ሽፋን በተመለከተ 38.40 በመቶ ሲሆን በከተማ 85.4 በመቶ፣ በገጠር ደግሞ 34.9 በመቶ ነው፡፡ የወረዳዎች ሽፋን በተመለከተም የ2ዐዐ1 ዓመት አፈፃፀም መሠረት በማድረግ ሌሞ 68 በመቶ ከፍተኛው ሲሆን ግቤ 11.66 በመቶ ዝቅተኛ ነው፡፡ የልማታዊ ባለሀብቶች ተሳትፎን ለማሳደግ በቀረቡ ማበረታቻዎች በመጠቀም በዞኑ የሚያበረታታ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ የዞኑን የመንገድ ልማት በተመለከተ በአሁኑ ወቅት 61 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ 22.9 ኪሎ ሜትር የተለያዩ ደረጃ ያላቸውና ለክረምትና በጋ የሚያገለግሉ የጠጠር መንገዶች እና 346 ኪሎ ሜትር የበጋ ጥርጊያ መንገዶች ብቻ ያሉ ሲሆን ዞኑ ካለው የቆዳ ስፋት፣ የህዝብ ብዛት፣ የልማትና የትራንስፖርት ፍላጎት አንፃር ሲታይ የመንገድ ሽፋኑ በጣም አነስተኛ ስለሆነ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላትና ከዞኑ ማኅበረሰብ ጋር በመቀናጀት ብርቱ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል፡፡ በዞኑ 4,5ዐዐ የመደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎች የሚገኙ ሲሆን ለ120 የገጠር ቀበሌያት ገመድ አልባ የስልክ መስማር ተዘርግቶ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። የሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚነትንና ሽፋንን በተመለከተ በሁሉም የዞኑ ገጠር ቀበሌያት ለመጠቀም የሚያስችል ኔትወርክ ዝርጋታ ተዘርግቶ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ከዘርፉ አገልግሎት ያገኛል። እንድሁም በሆሣዕና ከተማ፣ በወረዳ ከተሞችና በ18 የገጠር ቀበሌያት 65100 ነዋሪዎች የሃያ አራት ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

    046 555 3193
  • የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ

    Hawassa, Ethiopia

    በክልሉ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ፣ በህገ-መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክረሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ በማሳደግ ወንጀል ፈፃሚዎች ለህግ እንዲቀርቡና ለፈፀሙት ጥፋት በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም የህብረተሰቡንና የተቋማትን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም ነዉ፡፡

    046 220 7052
  • ስዌይንስ ሆቴል

    Hotels

    ስዌይንስ ሆቴል ላይ የእኛ ግብ በምትጠብቀው ማዶ ከአንተ ለማርካት ነው. የእኛ ምግባር ማሳየታችን አገልግሎት እና የመሰረተ ልማት ጥራት ለእኛ ጥሩ ስም አትርፈዋል. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን ማስያዣዎች ክፍል ያነጋግሩ.

    011 618 5878 www.greenlandtoursandhotels.com
  • TAMERE DEBEBE HOTEL

    Hotels

    046 555 2250