የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ
በከተሞች የልማት ሠራዊት ይገነባል ተብሎ የሚታመነውና እየተሠራም ያለው በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በትምህርትና በሰቪል ሰርቪስ ተቋማት ሲሆን ከኛ ተልዕኮ አንፃር በሰቪል ሰርቪሱ ተቋም ያለውን ፈጻሚ በጠንካራ የልማት ሠራዊት ከተገነባና በዚሁ የሚመራ ከሆነ ራሱን ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር አጽድቶ በእጁ ላይ ያለውን የህዝብ ሀብት (መሬት) በአግባቡ ልማት ላይ እንዲውል ያደረገዋል፣ የኢኮኖሚውን ተዋናዮችን በአግባቡ ይከታተላል፣ ይደግፈል፣ ውጤታማ ያደረገ በመሆኑም የኛ የወቅቱ ተልዕኮ ጠንካራ የልማት ሠራዊት መገንባት መሆኑን አምነን ለዚሁ ስኬት በሰፊው በማቀድ መተግበር ይኖርብናል፡፡