የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ስራ አመራር ተቋም በአዋጅ ቁጥር 89/2002ዓ/ም ተቋቋመ፡፡ ተልዕኮ፤ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙትን ተቋማት በሥራ አመራር መስክ ችግር ፈቺ የሆነ ጥናትና ምርምር በማድረግና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የሥልጠናና ምክር አገልገሎት በመስጠት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅማቸዉን ማጎልበት፡፡ ራዕይ በ2012 ዓ.ም በሀገራችን የላቀ የሥራ አመራር ልማት ማዕከል ሆኖ ማየት፣ እነዚህን ራዕይ እና ተልዕኮ በተሟላ መልኩ ለማሳካት የምንሰጣቸው ዋናዋና አገልግሎቶች፤ ስልጠናዎችን መስጠት እና ማስተባበር፣በለውጥ ፕሮግራሞች እና በአዳዲስ አስራሮች ዙሪያ የምክር አገልግሎት መስጠት፣ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ከማካሄድ ጎን ለጎን የመዝናኛ፣የመኝታ፣የካፍቴሪያ፣የቤተመጽሀፍት፣የኢንተርኔት፣የመማሪያክፍሎችእና የመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎቶች ሲሆኑ የሰው ሀብት በማልማት፣በጥናትና ምርምር ችግሮችን እየፈታን ለክልላችን እድገት የድርሻችንን ሀላፊነት ለመወጣት ለምናደርገው ጥረት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት/ድርጅቶች/ የአብረን እንስራ መልዕክታችን ይድረሳችሁ፡፡