Governmental Organizations
ኤጀንሲው ተልዕኮ /MISSION/
1. ስለ ኩነቶች ምዝገባ አገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ፣ የኩነቶች መረጃ በመልካም ፈቃደኝነት እና ተነሳሽነት የማስመዝገብ ባህልን ማጎልበት፣
2. ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የኩነቶች መረጃ በብቃትና በጥራት በመሰብሰብ ለፖሊሲ ቀረጻ፣ ለአገራዊ ስትራቴጂ አቅጣጫ እና ለማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም እንዲውል ማድረግ፣
3. በጥናትና ምርምር አዳዲስ የአሰራር ስልት በመቀየስ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ እና ዘመናዊ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት መገንባት ናቸው፡፡
የኤጀንሲው ዕሴቶች /Values/
ለዜጎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት፣ የበላይነት እና ተጠያቂነት የኩነቶች ምዝገባ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በክልላችን ማየት፣
የሕብረተሰቡን መረጃ ደህንነት መጠበቅ፣
• አገልጋይነት እና ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት፣
• ለሕዝብ ተጠያቂ መሆን፣• ሚስጥር ጠባቂነት፣
• በቡድን መስራት፣
• ሙያና ክህሎትን ለተጨባጭ ውጤት መጠቀም፣
• ጤናማና ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፣
• የሴቶችን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣
የምዝገባ ጊዜ
1. ከልደት በስተቀር ማንኛውም ወሳኝ ኩነት ሊያዘገይ የሚያስችል
በቂ ምክንያት ከሌለ በስተቀር በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ
አለበት፡፡
2. ማንኛውም ልደት ሊያዘገይ የሚያስችል በቂ ምክንያት ከሌለ
በስተቀር በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት፡፡
3. የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 በተደነገው
የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልተፈጸመ እንደሆነ አስመዝጋቢው
የዘገየበትን ምክንያት በማስረጃ ማስደገፍ አለበት፡፡