የፍለጋ ውጤቶች ለ - Debre Berhan

 • የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ

  Governmental Organizations

  የሰ/ሸዋ ዞን የቆዳ ስፋቱ 17,347.19 ስኬየር ኪ/ሜትር ሲሆን ከፍተኛ የሰብል፣ የእንስሳትና የደን ሀብት ክምሽት /potential/ አለው:: በተለይም በሰብል ልማት በብዕር፣ በጥራጥሬና ቅባት እህል በስፋት የሚመረት ሲሆን በ CSA መረጃ መሠረት በ 2ዐዐ5/2006 ምርት ዘመን 10,872,100 ኩ/ል ፣ በ 2ዐዐ6/2007 11,514,177፣ በ2007/2008 11,376,271 በ2008/2009 11,920,000 ተመርቷል፣ በተለይም ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሆን በተለይም የቢራ ገብስ በማምረት ለቢራ ፋብሪካዎች በማቅረብ የተሻለ ሥራ ተሰርቷልየዞኑን ሙሉ አቅሙን ለመጠቀም ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡በመስኖ እርሻ ልማትን ለማስፋፋት የከርሰምድርንና ከከርሰምድር በላይ ያለውን የውኃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፡፤ትላልቅ ግድቦችን በማስፋፋት ወንዞችን በመገደብና የጎርፍ ውኃን በማሰባሰብ ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅ ከፈተኛ ርብርብ በማድረግ የአትክልትና ፍራፍሬን ልማት እንዲስፋፋ ጥረት ተደረጓል፡፡በእንስሳት ዘርፍም በዳልጋ ከብት፣ በበግና ፍየል ዞኑ ትልቅ አቅም ያለው ሲሆን በተለይም ዞኑ እውቅና ያገኘበት የመንዝ በግ ዝርያ በስፋት በማርባትና በማድለብ ለዞኑ ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋፅኦ እየሰጠ ይገኛል ፡፡ እንዲሁም በወተትና በሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦ ሰፊ ድርሻ ያለው ሲሆን በማድለብ ረገድ የጅሩ ሰንጋ ዞኑ እውቅና ካገኝበት ተግባር አንዱ ነው፡፡ በደን ልማት ዞኑ ሰፊ ርብርብ ያደረገበት ሲሆን 6,604 ሄ/ር ስፋት ያለው የወፍ ዋሻ ደን፣የመንዝ ጓሳና በውስጡ የያዛቸው የቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ የዱር እንስሳት ባለቤት ነው፡፡ በተለይም በተለያዩ ጊዜ በተካሄዱ የተቀናጀ የደን ልማት ሥራና የማገዶ ተክል ኘሮጀክት በተሰሩ የተለያዩ የደን ማስፋት ሥራዎች ለዞኑ ትልቅ የደን ኢኮኖሚ ገቢ እንዲያበረክቱና ከደን ውጤቶች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ፋብሪካዎች እንዲከፈቱ ለዞኑ እድል ሰጥቷል፡፡

 • በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረ ብርሃን ጤና ሣይንሰ ኮሌጅ

  P.O.Box 37
  ኮሌጅ/ዩኒቨርሰቲዎች

  ኮሌጃችን ቀደም ሲል የደ/ብርሃን መለሰተኛ ጤና ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ት/ቤት ተብሎ በ1991 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በ1997 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ክልሉ የመንግስትና ጤና ጥበቃ ቢሮ በሰጡት ልዩ ትኩረት ወደ ጤና ኮሌጅነት በማሳደግ ሰያሜው የደብረብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በሚል እንዲጠራ ተደረገ፡፡ ኮሌጁ እስከ ሰኔ 2ዐዐ9 ዓ.ም ድረስ 3893 የጤና ባለሙያዎችን በተለያዩ ዲፖርትመንቶች አስመርቋል፡፡

 • ደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

  P.O.Box 20/21
  ኮሌጅ/ዩኒቨርሰቲዎች

  የደብረብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ ሲሆን በጥር ወር በ1949 ዓ.ም. በወቅቱ ፖይንት ፎር (Point Four) በመባል በሚታወቅ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አማካይነት የሕዝብ እድገት ት/ቤት በሚል ሥያሜ በቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ተመርቆ በ70 ተማሪዎች ሥራውን ጀመረ፡፡ ይህ ኮሌጅ በሀገራችን የመምህራን ሥልጠና ታሪክ ሁለተኛ ተቋም ሲሆን ላለፉት 60 ዓመታት በሠርቲፊኬትና በዲፕሎማ ደረጃ በርካታ መምህራንን በማስመረቅ ለሃገራችን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ • በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች በዲፕሎማ ደረጃ •የ1ኛ ደረጃ •የልዩ ፍላጎት እና •የቅድመ መደበኛ መምህራንን በማሠልጠን ላይ ይገኛል፡፡

 • በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ

  P.O.Box 146
  Governmental Organizations

  ተልእኮ፡ • ባልተማከለ የጤና አገልግሎት ስርዓት ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ፤ለሁሉም ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ የጤና ማበልጸግ፣በሽታ መከላከል፣የፈውስ ህክምናና የተሃድሶ የጤና አገልግሎት በመስጠትና በመቆጣጠር የዞኑን ሕዝብ ጤናና ደህንነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስነው፡፡ ራዕይ • የዞኑ ህዝብ ጤናማ፣አምራችና ብቁ ዜጋ ሆኖ ማየት የጤናው ዘርፍ የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ቁልፍ ገጽታዎች * ጥራትና ፍትሐዊነት፣ * ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎትና ተደራሽነት * ትራንስፎርሜሽን በተጨማሪም በዕቅዱ የዘርፉን ተልዕኮና ራዕይ ሊያሳኩ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸውን አራት የልህቀት ምሰሶዎች ተለይተዋል፤ 1. የላቀ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሁሉን አቀፍ ቀጣይነት፤ተደራሽነት፤ምላሽ ሰጪነት 2. የላቀ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያና ማረጋገጫ ውጤታማነት፣አዋጭነት፣ተቀባይነት ያለው/ ሕመምተኛ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ 3. የላቀ አመራርና አስተዳደር ፍትሀዊና ውጤታማ የሃብት አመዳደብ፤ የማህበረሰቡን የባለቤትነት መንፈስ ማጎልበት፤ወረዳን ትራንስፎርም ማድረግ፤አጋርነትና ትብብር 4. የላቀ የጤና ስርዓት አቅም ናቸው የሰው ኃብት፤የፋይናንስ፤የመሰረተ ልማት፤የተለያዩ ግብአቶች

 • አዲስ አምባ ሆቴል

  ሆቴል

  አዲስ አምባ ሆቴል የተሻለ ለማገልገል በባህር ዳር ውብ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሶስት ኮከብ ሆቴል ነው. የእኛ ትልቁ ንብረት አምባኤ ህንፃ ቀጥሎ, ቀበሌ 17 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ መንገድ ይገኛል