የፍለጋ ውጤቶች ለ - Assela

 • የፍቼ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

  Governmental Organizations

  የፍቼ ከተማ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ በ 112 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ የተመሰረተችው በ 1836 ዓ.ም ሲሆን የከተማዋ የአየር ንብረት ወይናደጋማ ሲሆን አመታዊ የዝናብ መጠኗ ከ 1200 እስከ 1300 ሚ.ሜ ነው፡፡

 • የምዕራብ ወልጋ ዞን አስተዳደር

  Governmental Organizations

  መግቢያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በግብርና መር ፖሊሲ የምትመራና ወደ ኢንዱሰትሪ መዋቅር ሽግግር በማድረግ ዕንቅስቃሴዋን እያፋጠነች መሆኗ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ያመላክታል፡፡ ይኸንን ዓላማ ለማሳካትና ያለውን እንድምታ ፈር ለማስያዝ ኢንዱሰትሪን ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ይታመንበታል፡፡ ስለዚህ ኢንዱሰትሪ ለመገንባት ከሚያስፈልጉ ነገሮችና አበይት ጉዳዮች ከሆኑት ውስጥ ምቹ መሬት፣ ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች መኖር፣ የሰው ኃይልና ካፒታል ወይም የፋይናንስ አቅም በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ቁምነገሮች ያቀፈ ዞን ወይም ክልል ደግሞ የኢንዱስትሪ ልማት ዕድል ለማግኘት ያለው ተስፋ ብሩህ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ይኽንን ዕውነታ በመንተራስ ዞናችንም ምቹ መሬት፣ የሰው ኃይልና ለኢንዱስትሪ ግብዓቶች የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች በሰፊው ያላትና ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ሥራዎች ተገምግሞ ሲታይ ያለው መረጃ ለአብነት እንደሚከተለው እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ስለዚህ ባለሀብቶች፣ ካምፓኒዮች፣የኒየኖች፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ዜግነት ያላቸው ተወላጆች በግልም ይሁን በቡድን በመደራገት ለኢንዱስትሪ ልማት ተለይተው የቀረቡትን ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎትና ዝግጁነት ላላቸው ሁሉ ዞናችን ተቀብላ ለማስተናገድ ጥሪዋን በአክብሮት ታቀርባለች፡፡

 • ኡኬ ከተማ አስተዳደር

  Governmental Organizations

  ራዕይ ከተማችን እስከ 2012 ዓ/ም በመሠረተ ልማት የተሟላች እንዲትሆንና የንግድ ማዕከልና የቱሪዠም መደረሻ ማድረግ ነው ተልዕኮ በየትኛውም አቅጣጫ መልካም አስተዳደር ለመስፋንና የፈጠንና መሠራተ ልማቶችን ተግባራዊ ማድራግ ኡኬ ከተማ አስተዳደር በ1999 ተመስርቶ በ2/11/1999 ህጋዊ ሰውነት ያገኘች ናት፡፡ የኡኬ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል በቀንድ ከብቶች ገበያ በሁለተኛ ደረጀ ላይ ትገኛለች፡፡

 • የሰቲት ሑመራ ከተማ አስተዳደር

  Governmental Organizations

  ራእይ በ2020 ዓ.ም መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ፍትህ የነገሰባት፣ዘላቂ ልማትና ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት በፕላን የምትመራ ውበትዋ የጠበቀች ለስራና ኑሮ ምቹ ከተማ ሆና ማየት፡፡ ተልእኮ በከተማዋ ያሉትን ሰብኣዊ እና ተፈጥሮኣዊ ሃብት አቀናጅቶ በመምራት ባለው መልኩ በስፋት ጥቅም ላይ በማዋልና የህዝቡ ማህበራዊና ቁጠባዊ ልማትን በማፋጠን መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራስያዊ ስርአት ግንባታ እንዲጎለብት ማድረግ፡፡ የሑመራ ከተማ አጠቃላይ መረጃ ሑመራ በ1890 ዓ.ም ነው የተቆረቆረችው፡፡ ከተማዋን መሰረቱ ተብለው በታሪክ የሚነገርላቸው ደሞ በተለያየ ምክንያት ከምዕራባዊ የአህጉራችን ክፍል ማለትም ቻድ ናይጀርያ ሴኔጋል ኩታ ገጠም ከሆነችው ጎረቤታችን ሱዳን እና ከደገማ የወልቃይት አካባቢ የመጡ ብሔረሰቦች መሆናቸው ይታመናል፡፡እነዚህ ከምዕራቡ የአህጉራችን ክፍል የመጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየተመናመነ የመጣ ቢሆንም አሁንምየማህበረሰቡ አካል ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ በሸክላ ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ለከተማዋ ስያሜ መነሻ ምክንያት የሆነው ሑመር ተብሎ የሚጠራ ዛፍ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ በብዛት ይገኛ እንደነበር እና የዛኔ ነዋሪዎች ሊገበያዩም ሆነ ለሌላ ጉዳይ መገናኘት ሲያስፈልጋቸው በዛ ዛፍ ስር ይገናኙ ስለ ነበረ በሂደት ሑመራ የሚል ሰያሜ ልታገኝ እንደቻለች የከተማዋ የዕድሜ ባለ ፀጋ ይናገራሉ፡፡ ሑመራ ከሱዳን ኤርትራ እንዲሁም ቃፍታ ሁመራ ወረዳ የምትዋሰን ስትሆን ከአ.አበባ 1100 ከ መቀሌ 585 ከጎንደር 255 ኪሎሜትር ርቃ ትገኛለች፡፡ ቆላማ የአየር ንበረት ያላት ስትሆን ከ520-620 ሜትር ከፍታ ከባሀር ጠለል አላት፡፡ የከተማዋ የህዝብ ብዛት ከ35 ሺ አካባቢ የደረሰ ሲሆን በተለይ በክረምትና መኸር ወቅት ለእርሻ የሚመጡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመላላሽ የቀን ሰራተኞች የምታስተናግድም ናት፡፡ ትግርኛ አማርኛ አረብኛ የከተማዋ ህዝብ መግባብያ ቋንቋዎች ናቸው፡፡

 • ወሊሶ ከተማ መስተዳደር

  ወሊሶ ከተማ ከአዲስ አበባ 114 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን, ከባሕር ወለል በላይ ወሊሶ መካከል ኢትዮጲያ. ቁመት ዋና ከተማ ዓመታዊ ዝናብ 1200mL ውድቀት እና 18-27 0c መካከል ሙቀት ጋር ስለ 1900 ሜትር ነው. ከተማ የተለያዩ ማኅበራዊ, ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ. በኩል ወሊሶ ከተማ አካባቢ 2,225.25 ሄክታር መሬት ሽፋን እና ብዛት ያለው ቅጽበት ካለፈ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ወሊሶ በ 1927 ተመሠረተ